Christ RIP
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ በተወዳጅ ሥራዎቹና በለዛ ባለው የድምፅ አወጣጡ የሚታወቀው ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት፣ ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
የሩሲያው ስፑትኒክ አፍሪካ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምንጮች ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ድምፃዊው ሆስፒታል ከመድረሱ በፊት ሕይወቱ አልፎ ነበር። እስካሁን ባለው መረጃም የድምፃዊው ትክክለኛ የሕልፈት ምክንያት በሕክምና ተጣርቶ በይፋ አለመገለጹ ተመልክቷል።
ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በኢትዮጵያ የሙዚቃ መድረክ ላይ የራሱን አሻራ ካሳረፉ የዘመኑ ድምፃውያን አንዱ ሲሆን፣ በተለይም «ሰላም አላት» እና «10 ከ10» የተሰኙ ሁለት የሙዚቃ አልበሞችን ለአድማጮቹ አበርክቷል። ከነዚህም ባሻገር «ግርማ ሞገሴ»፣ «የኔ ደሃ»፣ «የፍቅር ስጦታ» እና «አሁን አሁን» በተሰኙት ነጠላ ዜማዎቹና ሥራዎቹ በአድማጮች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝቷል።
ሚኪያስ በሙዚቃ ጉዞው ባህላዊ የኢትዮጵያ ቅኝቶችን ከዘመናዊ የሙዚቃ ቅንብር ጋር በማዋሐድ፣ እንዲሁም የፍቅርና የማኅበራዊ ሕይወት ገጽታዎችን በስሜት በመግለጽ ይታወቃል። ድንገተኛ ሕልፈቱ በኪነ ጥበብ ቤተሰቡና በአድናቂዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን የፈጠረ ሲሆን፣ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎች በቅርቡ ይፋ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
7
457
Anyways we a day away from GTA 6. Dont know how long amma be around for it but lets cook
Just stop
OFFICIAL: Gianluigi Donnarumma has been nominated for the 2026 @Globe_Soccer Best Goalkeeper award. Other nominees: Diogo Costa, Thibaut Courtois, Joan García, Gregor Kobel, Mike Maignan, Emiliano Martínez, David Raya, Matvey Safonov, Unai Simón.
4
253
What robert know bout pain n betrayal?
Robert Pattinson has been cast to play You (yes, You) in a biopic about your life.
(Source: @DEADLINE)
6
246





































